Surprise Me!

Aster Aweke-ሙዚቃ-music

2016-03-26 528 Dailymotion

===ሙዚቃ===
ከሰማይ ሰማያት፤ አድማሰን አስሰሽ፤
ስንት ከዋክብትን፤ ጨረቃን አዳርስሽ።
ምድርን በውብ ቋንቋ፤ በመንፈስ ያደልሽው፤
ሙዚቃ ነሽ ለዓለም፤ ፍቅርን ያለበስሽው።

ዓለም ሲያሸበርቅ፤ ሕይወትን አፍርቶ፤
ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ፤ እንደ ፀሃይ ፈክቶ።
የሰላም ነፀብራቅ፤ ፀዳል የወረሰው፤
ባንች ነው ሙዚቃ፤ አድማስ የታደሰው።

ከሰማይ ሰማያትን፤ አድማሰን አስሰሽ፤
ስንት ከዋክብትን፤ ጨረቃን አዳርስሽ።
ምድርን በውብ ቋንቋ፤ በመንፈስ ያደልሽው፤
ሙዚቃ ነሽ ለዓለም፤ ፍቅርን ያለበስሽው።

የሰው ልጅ በፍቅር፤ ወይ ባዘን ሲንካ፤
ኑሮውን በሚዛን፤ ሲፍትሽ ሲለካ።
ሲከፋው ሲደሰት፤ ሲናገር ከልቡ፤
ሙዚቃ ብቻ ነሽ፤ ስንቅና ቀለቡ።

ከሰማይ ሰማያትን፤ አድማሰን አስሰሽ፤
ስንት ከዋክብትን፤ ጨረቃን አዳርስሽ።
ምድርን በውብ ቋንቋ፤ በመንፈስ ያደልሽው፤
ሙዚቃ ነሽ ለዓለም፤ ፍቅርን ያለበስሽው።

Buy Now on CodeCanyon