Efrem Alemu New Mezmur
Buy the VCD to listen to more new efrem's song
GBU
Lyric: እረኛዬ (፪x) ፡ ነህ
እረኛዬ ፡ ነህ ፡ የነፍሴ ፡ ጠባቂን
ከአንበሳና ፡ ከድብ ፡ ከአውሬው ፡ ከነጣቂ

ያ ፡ ዳዊት ፡ እውነቱን ፡ እኮ ፡ ነው
ኧረኛዬ ፡ ብሎ ፡ የዘመረው
ከአንበሳ ፡ ከድብ ፡ ስታተርፈው
ያለአንተ ፡ ማን ፡ አስተዋሽ ፡ አለው
ገበታን ፡ አዘጋጀህለት
ንግስናን ፡ አንተው ፡ ስታነግሰው
ባይዘምር ፡ ይገርመኝ ፡ ነበር
የእኔም ፡ ታሪክ ፡ እንደዳዊት ፡ አለ

አባትዬ ፡ አባብዬ ፡ ነህ
አባትዬ ፡ ነህ ፡ የነፍሴ ፡ ጠባቂን
ከአንበሳና ፡ ከድብ ፡ ከአውሬው ፡ ከነጣቂ

መሰማሪያን ፡ ከአገኘሁ ፡ ቆየው
እረኛዬን ፡ ስለተጠጋሁ
በክንፎቹ ፡ ጥላ ፡ ስር ፡ ሆኜ
እኖራለሁ ፡ ተደላድዬ

(ለምን ፡ ቢባል) እረኛዬን ፡ ይዤ
(ለምን ፡ ቢባል) ቅጥሩን ፡ እዘላለሁ
(ለምን ፡ ቢባል) ሓሩሩ ፡ እንዳይጐዳኝ
(ለምን ፡ ቢባል) ጥላን ፡ አግኝቻለሁ (፪x)

አዝ፦ እረኛዬ (፪x) ፡ ነህ
እረኛዬ ፡ ነህ ፡ የነፍሴ ፡ ጠባቂን
ከአንበሳና ፡ ከድብ ፡ ከአውሬው ፡ ከነጣቂ

ከሰማይ ፡ ወደቀብኝ ፡ እጣ
እንዳትል ፡ ልዘምር ፡ ለጌታ
ጥሪ ፡ ነው ፡ የእርሱ ፡ ያደረገኝ
ለሌላው ፡ መሆን ፡ አቃተኝ
ከእናቴ ፡ ማህፀን ፡ ጀምሮ
የለየኝ ፡ ዘማሪ ፡ ነህ ፡ ብሎ
ዕድሜዬን ፡ ለእርሱ ፡ ሰጥቻለሁ
ሳመልከው ፡ ስዘምር ፡ እኖራለሁ

አባትዬ ፡ አባብዬ ፡ ነህ
አባትዬ ፡ ነህ ፡ የነፍሴ ፡ ጠባቂን
ከአንበሳና ፡ ከድብ ፡ ከአውሬው ፡ ከነጣቂ

ቸርነቱና ፡ ምህረቱ ፡ ሁልጊዜ ፡ ይከተሉኛል
በእግዚአብሔር ፡ ቤት ፡ ለዘላለም
እኖራለሁ ፡ ምን ፡ ያስፈራኛል

(እኔ ፡ አልፈራም) በትሩ ፡ ምርኩዞ
(እኔ ፡ አልፈራም) እነርሱ ፡ ያጽናኑኛል
(እኔ ፡ አልፈራም) ከፊቴ ፡ ገበታ
(እኔ ፡ አልፈራም) ተዘጋጅቶልኛል
(እኔ ፡ አልፈራም) ጽዋዬማ ፡ እርሱ ፡ ዘንድ
(እኔ ፡ አልፈራም) የተረፈ ፡ ነው
(እኔ ፡ አልፈራም) ኢየሱስን ፡ ይዤ
(እኔ ፡ አልፈራም) ምን ፡ እሆናለሁ